ባሕር ዳር: መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ጨዋታ አማኑኤል ገብረሚካኤል ጉዳት አስተናግዷል።
በሶከር ኢትዮጵያ መረጃ መሰረት ተጫዋቹ የገጠመው ጉዳት ከበድ ያለ በመኾኑ ለወራት ከሜዳ ያርቀዋል። የግራ እግሩ ሁለት አጥንቶቹ ስብራት የገጠመው አማኑኤል ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ ወራቶች እንደሚያስፈልጉት ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!