“የአፍሪካ ቡድኖች ከአሠልጣኞች በአጭር ጊዜ ውጤት መጠበቃቸው የአህጉሩን እግር ኳስ እንዳያድግ አድረጎታል” የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ

0
269

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቅጽል ስሙ የሃራምቤ ከዋከብት በሚል የሚጠራው የኬንያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ናቸው ኢንጂን ፊራት። እሳቸው እንዳሉትም የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ ቡድናቸው ውጤት ሲያጡ በችኮላ አሠልጣኛቸውን ከሥራ ያሰናብታሉ፤ ይህ የተሳሳተ ምልከታ ነው ብለዋል።

አሠልጣኙ “በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በጊዜ የተሰናበቱት ግብጽ፣ ጋና፣ ታንዛኒያ እና ቱኒዚያ ጨምሮ በርካታ ብሄራዊ ቡድኖች አሠልጣኞቻቸውን ያሰናበቱት በአጭር ጊዜ ዕቅድ ጥሩ ውጤት ከመጠበቅ ነው በማለት ማሳያ አቅርበዋል። “ይህ ዓይነቱ አሠራር ደግሞ የአህጉሩን የእግር ኳስ ዕድገት ከመጉዳቱ በተጨማሪ የረጅም ጊዜ ስኬትን አያስገኝም” ብለዋል።

የተርክዬ ዜጋ የኾኑት ኢንጂን ፊራት የሀገራቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች አሠልጣኝ ከማባረር ‘ብሔራዊ ቡድኑ ምንድን ነው የጎደለው? ምንስ ተጨማሪ ነገር ይቅረብለት?’ ብሎ በመጠየቅ እና ተደጋግፎ ለተጫዋቾች ብሔራዊ ስሜትን በማስረጽ በረዥም ጊዜ ቆይታ ጥሩ ቡድን እንዲመሰርቱ እድል ሊሰጣቸው ይገባል ሲል የዘገበው ፕልዝ ስፖርትስ ነው።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here