ኢትዮጵያ በውኃ ዋና ስፖርት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡

0
308

ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በውኃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 8ኛው የዞን 3 አፍሪካ ውኃ ዋና ሻምፒዮና በማስተርስ ዋና ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በዞን 3 የአፍሪካ ውኃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር በታዳጊ ወጣቶች እና በማስተርስ ዋና ውድድር ተሳትፋ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና በ100 ሜትር ደረት ቀዘፋ በአትሌት እስከዳር አቻምየለህ አማካኝነት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here