ታንዛኒያ በዘመናዊነቱ በምሥራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የኾነ ስታዲየም ልትገነባ መኾኗን አስታወቀች።

0
247

ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአሩሻ ከተማ ለሚገነባው የእግር ኳስ ስታዲየም የታንዛኒያ መንግሥት 286 ቢሊዮን ሽልንግ መመደቡን አስታውቋል።

ይህ በቻይናው “ሬል ዌይ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሊሚትድ” የሚገነባው ዘመናዊ ስታዲየም በፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ስም የሚሰየም ይኾናል ተብሏል። የሀገሪቱ የባሕል፣ ስነ ጥበባት እና ስፖርት ሚኒስትር ደማስ ንዱምባሮ ከሰሞኑ እንዳሉት ስታዲየሙ 30ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ሲኖረው፤ በዘመናዊነቱ ደግሞ በምሥራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም ይኾናል ብለዋል።

የስታዲየም ግንባታው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2025 ይጠናቀቃል ነው የተባለው። ታንዛኒያ በ2027 የሚደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ከኬንያ እና ኡጋንዳ ጋር በሦስትዮሽ እንደሚያዘጋጁ ዘ ሲቲዝን ድረ ገጽ አስታውሷል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here