ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጋና እየተከናወነ በሚገኘው 13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳልያ እና 3ኛውን የብር ሜዳልያ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አስመዝግባለች።
በውድድሩ አትሌት ንብረት መላክ በ29:45.37 በቀዳሚነት ውድድሩን አጠናቅቋል። አትሌት ገመቹ ዲዳ በ29:45.68 የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወድድሩን ፈፅሟል። ኬንያዊው ኢቫንስ ኪፕቱም በ29:47.61 በሦስተኛነት ውድድሩን ጨርሶ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝቷል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኃይለማርያም አማረ 29:57.39 የሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ወድድሩን ፈፅሟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!