ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በአጠቃላይ 19 አትሌቶች የሚፎካከሩ ሲኾን ኢትዮጵያ በሦስት አትሌቶች ትወከላለች። በርቀቱ 27 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ የግሉ ምርጥ ሰዓት ባለቤት የኾነው አትሌት ገመቹ ዲዳ የማሸነፍ ቅድመ ግምት ካገኙ ተፎካካሪዎች ይገኝበታል።
ኃይለማርያም አማረ እና ንብረት መላክ ሌሎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው። አትሌት ኃይለማርያም ከአራት ዓመት በፊት በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደ የአፍሪካ ጨዋታዎች በ3 ሺህ መሰናክል ለሀገሩ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቶ ነበር። ከዚህም በተማሪ በ2022ቱ የሞሪሽየስ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ መሰናከል እና በ5 ሺህ ሜትር የድርብ ድል ባለቤት መኾን የቻለ ጠንካራ አትሌት ነው።
በምሽቱ ሩጫ የኬንያ እና የኤርትራ አትሌቶች ዋነኞቹ የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተፎካካሪ እንደሚኾኑ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!