ሲሳይ ለማ በማራቶን ታሪክ ፈጣኑን አራተኛ ሰዓት አስመዘገበ።

0
298

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ረፋዱን በስፔኗ የባሕር ዳርቻ ከተማ ቫሌንሲያ በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ በድንቅ ብቃት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፍ ችሏል።

የ2021 ሎንዶን ማራቶን አሸናፊው ሲሳይ ለማ የዛሬውን ቫሌንሲያ ማራቶን ለመጨረስ 2:01:48 ሰአት ፈጅቶበታል። በዚህም ሲሳይ ለማ በማራቶን ታሪክ ፈጣኑን አራተኛ ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል።

ውድድሩን በሁለተኛነት ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ ጨርሷል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዳዊት ወልዴ ሦስተኛውን ቦታ በመያዝ አጠናቋል።

በውድድሩ ተካፋይ የነበረው የ41 አመቱ ቀነኒሳ በቀለ በአራተኛነት ውድድሩን ጨርሷል።

2:04:19 በሆነ ሰአት ያጠናቀቀው ቀነኒሳ የአለም የአንጋፋዎችን የማራቶን ክብረወሰን ሰብሯል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here