17ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተራዘመ፡፡

0
395

ባሕር ዳር: መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 17ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን ከተማ ሊካሄድ የነበረው ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አትሌቲክስ ፌደሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

“የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መጋቢት 15/2016 ዓ.ም በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ሊካሄድ የነበረው 17ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መኾኑን እንገልጻለን” ብሏል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here