ባሕር ዳር፡ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሊቨርፑል፣ የቼልሲ እና የኒውካስትል አሠልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ከስምንት ወራት ቆይታ በኋላ ከስፔን ላ ሊጋ ቡድን ሴልታ ቪጎ መልቀቃቸው ተሰምቷል ።
ቤኒቴዝ ሴልታ ቪጎን የተረከቡት በሰኔ ወር ላይ ነበር። ኾኖም ቡድኑ በእሳቸው እየሠለጠነ ከ33 ጨዋታዎች ዘጠኙን ማሸነፍ ችሏል።
ቡድኑ ባወጣው መግለጫ “ራፋኤል ቤኒቴዝ በፍፁም ቁርጠኝነት እና ትጋት ቢሠሩም የሚጠበቀውን ውጤት አላመጡም። እናም ከረዳቶቻቸው ጋር ላሳዩት ተሳትፎ፣ ታማኝነት እና ሙያዊ ብቃት እንዲኹም ያላሰለሰ ሥራ ልባዊ ምስጋና ማቅረብ እንፈልጋለን፤ መልካም እድል እና ስኬትም እንመኝላቸዋለን” በማለት አትቷል።
ቤኒቴዝ የእንግሊዝን ብሔራዊ ቡድን ሊያሠለጥኑ ይችላሉ የሚሉ ጭምጭምታዎች በስፋት እየወጡ ይገኛሉ።ሴልታ ቪጎ በላሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ በ24 ነጥብ በ17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲል የዘገበው ዘ ሚረር ነው፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!