ሁሉም ክፍት የሆነ የግል የበላይነት ዓመታዊ የቼዝ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ።

0
278

ባሕር ዳር: መጋቢት 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የ2016 ለሁሉም ክፍት የሆነ የግል የበላይነት ዓመታዊ የቼዝ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት ፍጻሜውን አግኝቷል።

ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው በዚህ ሻምፒዮና በወንዶች ዮሴፍ ክፍሌ 1ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ለይኩን መስፍን እና ያለም ዘውድ መኮነን ከ2 እስከ 3 ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል። በሴቶች ልደት አባተ፣ አስቴር መላከ እና መቅደስ ደምሴ ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል።

በሁለቱም ፆታ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ሲካሄድ በቆየው ሻምፒዮና ለአሸናፊዎች በየደረጃቸው ከሜዳሊያ በተጨማሪ ከ5ሺህ እስከ 15ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ተበርክቶላቸዋል።

ለሁሉም ክፍት በሆነው በዚህ ሻምፒዮና አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሀገራቸውን በመወከል በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንደሚሳተፉ ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ይገልፃል።
የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው በዚህ ዓመታዊ ሻምፒዮና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ 103 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

ለሁሉም ክፍት በሆነው የግል የበላይነት ሻምፒዮና ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጸደቀ ይሁኔ እንዲሁም የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል የኢትዮጵያ ባሕል እና ስፓርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here