በረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ምስል የታተመው ቴምብር ይፋ ኾነ።

0
283

ባሕርዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፖስታ በረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ምስል ያሳተመውን ቴምብር ይፋ አድርጓል። አትሌቷ ለሀገር የዋለችውን ውለታ ታሪክ የማይረሳው መኾኑን ተከትሎ በስሟ ቴምብር መታተሙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ፖስታ ሀገሪቱ ያላትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በቴምብር በማሳተም ሲያስተዋውቅ ቆይቷል።

ሴቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ጉልህ ተሳትፎ እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ያነሳው የኢትዮጵያ ፖስታ፤ የኢትዮጵያ ኩራት የኾነችውን አትሌቷንም በቴምብር ምልክቱ አኑሯታል።
የኢትዮጵያ ፖስታ፤ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ መጀመሪያ ካሸነፈችበት ኦሎምፒክ አኹን እስካለችበት ኅላፊነት ድረስ የሚገልጹ ምስሎች በቴምብር አሳትሟል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here