ባሕር ዳር: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ግላስጎው አቅንቷል፡፡
19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 3 ቀን 2024 በግላስጎው እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ ለሚካፈለው የልዑካን ቡድንም ዛሬ ዕኩለ ቀን ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!