የባየርሙኒኩ ተከላካይ አልፎንሶ ዴቪስ ሪያል ማድረድን ሊቀላቀል ነው።

0
256

ባሕርዳር: የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሪያል ማድሪድ በቅርቡ ፈረንሳዊ ኮከብ ኪሊያን ምባፔን በመጭው ክረምት የግሉ ማድረጉ ተረጋግጧል።እንደ ጎል ዘገባ ከኾነ የባየርሙኒኩ የግራ መስመር ተከላካይ አልፎሶ ዴቪስም ነጮችን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ተስማምቷል።

ካናዳዊ ተጫዋች በባየርሙኒክ የሚያቆየው ውል ከዓመት በኃላ ይጠናቀቃል።ውሉን ለማራዘምም ፈቃደኛ አልኾነም። በመኾኑም በሚቀጥለው ክረምት ባየርሙኒክ አልፎንሶን ለማድሪድ የማይሸጥ ከኾነ በሚቀጥለው ዓመት በነጻ የሚያጣው ይኾናል።

አልፎንሶ ዴቪስ አሁን ላይ በጥራት ከሚጠቀሱ የግራ ተከላካዮች መካከል አንዱ ነው።በረያል ማድሪድ እና ተጫዋቹ ወረቀት ላይ ያልሰፈረ ስምምነት መሰረትም የ23 ዓመቱ ኮከብ ነጩን መለያ መልበሱ እርግጥ ነው።ምንም እንኳ መቼ የሚለው የጊዜ ጉዳይ ቁርጥ ብሎ የተቀመጠ ባይኾንም።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here