ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ የመጀመርያ ጨዋታ ወደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሜዳ ያመራው አርሰናል አሸንፎ ተመልሷል።
አርሰናል ስፖርቲንግ ሊዝበንን 1ለ0 በኾነ ጠባብ ውጤት ነው ያሸነፈው፡፡
የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ካይ ሀቨርዝ አስቆጥሯል፡፡
በሌላ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ የመጀመርያ ጨዋታ ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን አሸንፏል።
ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 2ለ1 ነው ማሸነፍ የቻለው።
በሳንቲያጎ ቤርናባው በተደረገው ጨዋታ የባየር ሙኒክን ግቦች ሉዊስ ዲያዝ እና ሃሪ ኬን አስቆጥረዋል፡፡
ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት ያልታደገች ግብን ኬሊያን ምባፔ አስቆጥሯል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



