ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛው የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች እና በ19ኛው የባሕል ፌስቲቫል የገና ስፖርት ፍፃሜውን አግኝቷል።
ውድድሩ ላይ አራት ተሳታፊዎች ለአሸናፊነት በዙር ተጫውተዋል።
ዛሬ ሦሥተኛ ጨዋታዎች ሲደረጉ አማራ ክልል አዲስ አበባን 2ለ1 አሸንፏል።
ይህ ድል አማራ ክልል በሰባት ነጥብ በገና ስፖርት አጠቃላይ አሸናፊ አድርጎታል።
ሀረሪ ክልልን 6ለ0 ያሸነፈው ኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ ኾኖ ውድድሩን ጨርሷል።
አንድ ጨዋታ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ የተለያየው እና በአንዱ የተሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ደግሞ ሦሥተኛ ኾኖ ውድድሩን አጠናቅቋል።
ዘጋቢ፦ ኃይሉ አዳነ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



