ብርኖ ፈርናዴስ የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ኾኖ ተመረጠ።

0
5

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው ፈርናዴስ የመጋቢት ወር የእንግሊዝ ፕምዬር ሊግ ምርጥ ተጫዋች ኾኖ ተመርጧል።

አማካዩ በመጋቢት ወር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አራት ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ፕሪምዬር ሊጉ በድረ ገጹ ባጋራው መረጃ ብርኖ ፈንናዴስ በአስደናቂ የብቃት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ክብረ ወሰን የጨበጠው ፈርናዴስ በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን የተመዘገበውን ኳስ አመቻችቶ የማቀበል ክብረ ወሰን የመስበር ዕድል እንዳለውም ጽፏል።

በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ ቴሪ ዳኔል ሄነሪ እና ኬቨን ዲብሮይን በአንድ የውድድር ዘመን 20 ኳሶችን አመቻችተው በማቀበል ባለ ክብረ ወሰን ናቸው።

ሰባት ጨዋታዎች በሚቀሩት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዘመን ብርኖ ፈርናዴስ 16 ግቦችን አመቻችቶ አቀብሏል።

በማይክል ካሪክ ሥር አስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው አማካዩ እያሳየው በሚገኘው ብቃት በቀሪ ጨዋታዎች ክብረ ወሰኑን የመጋራት ዕድል፤ ከዚያም ባሻገር ክብረ ወሰኑን የመስበር ዕድል እንደሚኖረው የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ በድረ ገጹ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።

የመጋቢት ወር የወሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው ፈርናዴስ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በርካታ ጊዜ የወሩ ምርጥ ተጫዋቾች ተብለው ከተመረጡ ተጨዋቾች መካከል አንደኛው ኾኗል።

በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ ሰርጂዮ አጉዬሮ፣ ሀሪ ኬይን እና ሞሐመድ ሳላህ እያንዳንዳቸው ሰባት ሰባት ጊዜ በመመረጥ ቀዳሚዎች ናቸው።

ብርኖ ፈርናዴስ፣ ስቴቨን ጄራርድ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ጊዜ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል ይከተላሉ።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here