በርናንዶ ሲሊቫ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲን ይለቃል።

0
6

 

ባሕርዳር፡ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም(አሚኮ) የ31 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ አማካይ በርናንዶ ሲሊቫ በማንቸስተር ሲቲ ያለው ቆይታ በውድድሩ መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል። ተጫዋቹ በሰኔ ወር መጨረሻ ኮንትራቱ ሲያበቃ ክለቡን በነፃ ዝውውር ይለቃል ተብሏል።

ሲሊቫ ቀጣይ ርምጃው ምን እንደሚኾን “በእርግጠኝነት” እንደሚያውቅ ገልጿል። ነገር ግን አሁን ላይ ትኩረቱ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የውድድር ዘመኑን በስኬት ማጠናቀቅ መኾኑን ተናግሯል።

ወኪሎቹ ከሌሎች ክለቦች ለተጫዋቹ ያለውን የፍላጎት ጥያቄ መቀበል ጀምረዋል። ባርሴሎና፣ ጁቬንቱስ እና የቀድሞ ክለቡ ቤንፊካ ዋነኛ ፈላጊዎቹ እንደኾኑም እየተነገረ ነው።

ከሳዑዲ አረቢያ እና ከአሜሪካ ክለቦችም ፍላጎቶች አሉ ተብሏል።

የበርናንዶ ሲሊቫ መልቀቅ ለማንቸስተር ሲቲ አማካይ ክፍል ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል። ማንቸስተር ሲቲ የመሐል ሜዳውን ለማጠናከር ወደ ገበያ እንደሚወጣ ይጠበቃል።

ተጫዋቹ እ.አ.አ. በ2017 ማንቸስተር ሲቲን ከተቀላቀለ ጀምሮ በክለቡ ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ ከኾኑ ተጫዋቾች አንዱ ለመኾን በቅቷል። ቢቢሲ እንደዘገበው በዚህ ቆይታውም ከ18 በላይ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here