የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከኀላፊነታቸው ለቀቁ።

0
5

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋብርኤል ግራቪና ከኀላፊነታቸው ለቀቁ።

የዓለም ዋንጫ የአራት ጊዜ አሸናፊዋ ጣሊያን ለሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ሳትሳተፍ በመቅረቷ ነው ከኀላፊነታቸው የለቀቁት።

ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደዘገበው ውሳኔው ጣሊያን ዓለም ዋንጫ ማሳተፍ ሳትችል መቅረቷን ተከትሎ የመጣ ነው ብሏል።

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቱ ብቻ ሳይኾን የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ጄናሮ ጋቱሶም ከኀላፊነታቸው ሊለቁ እንደሚችሉ ፋብሪዚዮ ጽፏል።

ዋንስፖርት የጣሊያን እግር ኳስ በተቋማዊ ውድቀት ውስጥ እንደሚገኝ ዘግቧል። የፕሬዝዳንቱ መልቀቅም በጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት ምክንያት ነው ብሏል። የጣሊያን እግር ኳስ ጥልቅ ለውጥ እንደሚያስፈልገውም አመላክቷል።

ፕሬዝዳንቱ እ.አ.አ በ2018 ጀምሮ በጣሊያን እግር ኳስ ውስጥ ከፍተኛውን ሥፍራ ይዘው ቆይተዋል። በሥልጣን ዘመናቸው እ.አ.አ በ2020 የአውሮፓ ሀገራት ዋንጫን አሸንፈዋል።

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን በ2022 እና በ2026 የዓለም ዋንጫ መሳተፍ አልቻለም። እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ ለ2018 ለዓለም ዋንጫ መሳተፍ አልቻለችም።

ጣሊያን ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው በ2014 የብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ነው። ፉትቦል ኢታሊያ በዘገባው የጣሊያን እግር ኳስ ከእንደገና መገንባት አለበት ብለዋል።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here