ኢትዮጵያ በፊፋ የዓለም የእግርኳስ ደረጃ ሦሥት ደረጃዎችን አሻሻለች::

0
5
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፊፋ የዓለም የእግርኳስ ደረጃ ይፋ ሲደረግ ኢትዮጵያ ሦሥት ደረጃዎችን አሻሽላለች።
ኢትዮጵያ ከነበረችበት 147ኛ ደረጃ ወደ 144ኛ ደረጃ ከፍ ብላለች። ዋሊያው በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን በደርሶ መልስ 4ለ0 በኾነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
በአፍሪካ ደረጃ ሞሮኮ ቀዳሚ ስትኾን ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሴኔጋል፣ ናይጀሪያ እና ግብጽ ደግሞ 14ኛ፣ 26ኛ እና 30ኛ ደረጃን ከዓለም ሲይዙ ከአፍሪካ በቅደም ተከተል እስከ አራተኛ ተቀምጠዋል::
በመጋቢት ወር ደረጃ መሠረት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ቁንጮነትን ዳግም ተቆናጥጧል። ስፔን እና አርጀንቲና ደግሞ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንግሊዝ፣ ፖርቹጋል፣ ብራዚል፣ ኔዘርላንድ፣ ሞሮኮ፣ ቤልጅየም እና ጀርመን በቅደም ተከተል እስከ 10ኛ ደረጃ ይዘዋል።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኀይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here