ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል
16 ሀገራትን ያፎካከረው የምሽቱ ጨዋታ ስምንቱን አሰናብቶ ስምንቱን ወደ ሚቀጥለው ዙር አሳልፏል።

ቱርክዬ ሮማንያን 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።

ጣሊያን ሰሜን አይርላንድን 2ለ0 አሸንፋለች።

ዩክሬን በሲዊድን 3ለ1 ተሸንፋለች።

በመደበኛው እና በጭማሪ 30 ደቂቃ የጨዋታ ሰዓት 1ለ1 የተጠናቀቀው የዌልስ እና የቦሲናያ እና ኤርዜጎቪና ጨዋታ ወደ መለያ ምት አምርቷል። በመለያ ምትም ቦሲናያ እና ኤርዜጎቪና ዌልስን 4ለ2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።

ዴንማርክ ሰሜን መቄዶኒያን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። ጨዋታው በዴንማርክ 4ለ0 አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው።

ፖላንድ አልቤኒያን 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።

ስሎቫኪያ በኮሶቮ 4ለ3 ተሸንፋለች።

በመደበኛው እና በጭማሪው 30 ደቂቃ የጨዋታ ሰዓት 2ለ2 የተጠናቀቀው የቼክ ሪፐብሊክ እና የአየርላንድ ጨዋታ ወደ መለያ ምት አምርቷል። በተሰጠው መለያ ምትም ቼክ ሪፐብሊክ እና አየርላንድን 4ለ3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።
ወደ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ጨዋታዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል። በመጨረሻው ጨዋታ ድል የሚቀናቸው አራት ሀገራት የዓለም ዋንጫው ተሳታፊ ይኾናሉ። በመጨረሻው ጨዋታም:-

ኮሶቮ ከ ቱርክዬ

ሲዊዲን ከ ፖላንድ

ቼክ ሪፐብሊክ ከ ዴንማርክ

ቦሲናያ እና ኤርዜጎቪ ከ ጣሊያን ጋር ይጫወታሉ።
የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለ ድሏ ጣሊያን የመጨረሻውን ጨዋታ ድል ካደረገች ከዓመታት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ መድረክ ትመለሳለች።