የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጋቶች ፓኖም ወደ ሞሮኮ አይጓዝም።

0
32
ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጋቶች ፓኖም በሀዘን ምክንያት ወደ ሞሮኮ እንደማይጓዝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ይጫወታል። የመጀመሪያ ጨዋታውንም በሞሮኮ ያደርጋል። ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው ወደ ሚደረግባት ሀገር ሞሮኮ ዛሬ ይጓዛል። የቡድኑ አማካይ ጋቶች ፓኖም ከጉዞው መቅረቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የኾነው ጋቶች ፓኖም በወላጅ አባቱ ድንገተኛ ሕልፈት ምክንያት ወደ ሞሮኮ ከሚጓዘው ልዑክ ሳይካተት መቅረቱን ፌደሬሽኑ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት በጋቶች ፓኖም ወላጅ አባት ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here