በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ፣ አርሰናል እና ፒኤስጂ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ።

0
42

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል።

በመጀመሪያው ጨዋታ በቦዶ ጊሊምት 3ለ0 የተሸነፈው ስፖርቲንግ ሊዝበን በመልሱ ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ውጤቱን ቀልብሶ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ስፖርቲንግ ሊዝበን 5ለ0 በኾነ ውጤት በማሸነፍ ነው ውጤቱን የቀለበሰው።

ተጠባቂው የማንቸስተር ሲቲ እና የሪያል ማድሪድ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ከሪያል ማድሪድ ጋር የተጫወተው ማንቸስተር ሲቲ በድምር ውጤት ተሸንፎ ከፉክክሩ ሲሰናበት የመድረኩ ንጉሥ ሪያል ማድሪድ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተሸጋግሯል።

በመጀመሪያው ጨዋታ ወደ ጀርመን አቅንቶ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር 1ለ1 የተለያየው አርሰናል በመልሱ ጨዋታ በሜዳው 2ለ0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ቸልሲ እና ፒኤስጂ ያደረጉት ጨዋታ በፒኤስ ጂ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ወደ ፈረንሳይ አቅንቶ 5ለ2 ተሸንፎ የተመለሰው ቸልሲ በመልሱ ጨዋታ ደግሞ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 3ለ0 ተሸንፏል።

ሁለት የእንግሊዝ ክለቦች ማንቸስተር ሲቲ እና ቸልሲ
በአንድ ቀን ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሰናብተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here