ብርቱ ፉክክር የሚደረግበት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዛሬ ጨዋታ።

0
56
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራት የደርሶ መልስ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ከደርሶ መልስ ጨዋታዎች መካከል ተጠባቂው የማንቸስተር ሲቲ እና የሪያል ማድሪድ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ምሽት 5፡00 ላይ ይካሄዳል።
ወደ ስፔን ተጉዞ በመድረኩ ንጉሥ ሪያል ማድሪድ 3ለ0 የተሸነፈው ማንቸስተር ሲቲ ዛሬ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ውጤቱን ለመቀልበስ ታላቅ ፍልሚያ ያደርጋል። ማንቸስተር ሲቲ ውጤቱን ለመቀልበስ ከሦስት በላይ ግቦችን ማስቆጠር ይኖርበታል። ይህ ብቻ አይደለም ግብ እንዳይቆጠርበትም ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ማድሪድ በዛሬው ጨዋታ ቀድሞ ግብ ካስቆጠረ የማንቸስተር ሲቲ የማለፍ እድል የበለጠ ይጠባል።
ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ካለው ታሪክ እና የመጀመሪያውን ጨዋታ ካሸነፈበት ብቃት አንጻር ማንቸስተር ሲቲ የዛሬውን ጨዋታ ለመቀልበስ አዳጋች እንደሚኾንበት ይጠበቃል።
ወደ ጀርመን ተጉዞ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር 1ለ1 የተለያየው አርሰናል ዛሬ በሜዳው የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል። ወሳኙ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት 5፡00 ይደረጋል።
ለአራት ዋንጫዎች እየተፎካከረ የሚገኘው አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ ይጠበቃል። ነገር ባየር ሌቨርኩሰንም በመጀመሪያው ዙር ካሳየው ብቃት አንጻር በቀላሉ እጅ ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም።
በሻምፒዎንስ ሊጉ የጥሎ ማለፍ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲካሄዱ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ በፒኤስ ጂ 5ለ2 የተሸነፈው ቸልሲ ዛሬ ውጤቱን ቀልብሶ ለማለፍ ምሽት 5፡00 ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በቦዶ ጊሊምት 3ለ0 የተሸነፈው ስፖርቲንግ ሊዝበን ምሽት 2፡45 በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ክስተት የኾነው ቦዶ ጊሊምት በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ የማለፍ እድሉን አስፍቶ ነው የመጣው።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here