ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየምን ከደረሰበት ጉዳት ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የከተማ አሥተዳደሩ ስታዲየሙን ከሦሥተኛ ወገን ነጻ በማድረግ ጥገና እንዲደረግለት ለክልሉ መንግሥት
ርክክብ አድርጓል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ስታዲየሙ በፈጣን ሁኔታ ጥገናው ተከናውኖ ወደ ሥራ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ሁኔታዎች ሁሉ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።
የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋዬ በስታዲየሙ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ጥገናውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ስታዲየሙን ለአገልግሎት ለማብቃት ቢሮው በቁርጠኝነት ወደ ሥራ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ከወልድያ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ስታዲየሙ ወደ አገልግሎት መመለሱ በከተማዋ እና በአካባቢው ለሚገኘው የስፖርት ቤተሰብ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



