ቼልሲ የገንዘብ እና የተጫዋቾች የዝውውር እገዳ ቅጣት ተጣለበት።

0
44

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቸልሲ እ.አ.አ ከ2011 እስከ 2018 በክለቡ ተፈጽመዋል በተባሉ “ሚስጥራዊ ክፍያዎች” ምክንያት እየገዳ ተጥሎበታል።

ቸልሲ ከክለቡ ጋር ግንኙነት ላላቸው ለሦስተኛ ወገኖች ያልተገለጹ ክፍያዎች፣ ለተጫዋቾች፣ ላልተመዘገቡ ወኪሎች እና ለሌሎች ሕጋዊ ያልኾኑ አሠራሮችን በመከተል ክፍያ መፈጸሙን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህም መሠረት ቼልሲ የገንዘብ ቅጣት እና የተጫዋቾች ዝውውር እገዳ ተጥሎበታል ነው የተባለው።

ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የታወቀው በ2022 ክለቡን የገዙት አሜሪካውያን ባለሀብቶች በክለቡ ላይ ባደረጉት የፋይናንስ ምርመራ ወቅት እንደነበር ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here