የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ከተማ ደመቀ።

0
60

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በሴዑል ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ነግሠዋል።

ዛሬ በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ማራቶን በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም አንደኛ በመውጣት ነው የነገሡት።

በወንዶች ውድድር አትሌት ሀፍቱ ተከሉ 2፡04፡23 በኾነ ሰዓት በመግባት ለሁለተኛ ጊዜ ክብሩን ሲቀዳጅ፣ ጌታነህ ሞላ ሁለተኛ፣ ፀጋዬ ታደሰ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በሴቶች ውድድርም አትሌት ሔቨን ኃይሉ 2፡19፡10 በኾነ የግል ምርጥ ሰዓቷ አንደኛ የወጣች ሲኾን በቀለች ጉደታ እና ቦሰና ሙላቴ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦሥተኛ በመኾን ውድድሩ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዲደምቅ አድርገዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here