ባሕር ዳር፡ መጋቢት 04/2018 ዓ.ም(አሚኮ) የማንቸስተር ሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ የየካቲት ወር ምርጥ አሠልጣኝ ተብለው ተመርጠዋል።
አሠልጣኙ በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ ለበርካታ ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ ተብለው የተመረጡ ሦሥተኛው አሠልጣኝ ኾነዋል።
በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ ለበርካታ ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ በመባል ክብረ ወሰን የያዙት የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ናቸው። ታሪካዊው አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ 27 ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ ተብለው ተመርጠዋል።
የቀድሞው የአርሰናል አሠልጣኝ አርሰን ቪንገር 15 ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ በመባል በታሪክ ሁለተኛው አሠልጣኝ ናቸው።
ፔፕ ጋርዲዮላ ደግሞ 12 ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ በመባል በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ታሪክ ሦሥተኛው አሠልጣኝ መኾናቸውን ፕሪምዬር ሊጉ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
የወቅቱ የኤቨርተን አሠልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በፕሪምዬር ሊጉ 11 ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ በመባል አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የቀድሞው የሊቨርፑል አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ ደግሞ 10 ጊዜ የወሩ ምርጥ አሠልጣኝ በመባል በታሪክ አምስተኛው አሠልጣኝ ናቸው።
የማንቸስተር ሲቲው ተጫዋች አንቶኒ ሴሚንዮ ደግሞ የየካቲት ወር ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



