ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቸልሲ የአምበሉን ሬስ ጀምስን ውል እስከ ሰኔ/2032 ድረስ አራዝሟል።
ቸልሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ አምበሉ ሬስ ጀምስን እስከ 2032 ድረስ አዲስ ውል በመፈራረሙ ደስተኞች ነን ብሏል። ጀምስ መሪ ነው ያለው ክለቡ ውሉን በማራዘሙ ኩራት እንደሚሰማው አስታውቋል።
በቸልሲ አካዳሚ ያደገው ጀምስ አስደናቂ ተጫዋች መኾኑን አስመስክሯል። በቸልሲ መለያ ከ200 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገው ተጫዋቹ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ የፊፋ ክለብ የዓለም ዋንጫን እና ሌሎች ዋንጫዎችን ከቸልሲ ጋር አሳክቷል።
ጀምስ ከ50 ጨዋታዎች በላይ ቸልሲን በአምበልነት መርቷል።
አምበሉ ሬስ ጀምስ በሚወደው ክለቡ ውስጥ ውል በማራዘሙ ደስተኛ መኾኑንም ገልጿል።
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



