በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
45
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 04/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
የፋሲል ከነማ እና የመቻል ጨዋታ ዛሬ ከሚዳርጉ ጨዋታዎች መካከል አንደኛው ነው። ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ቀን 9፡00 ላይ ይደረጋል።
ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ጋር ከተለያየ በኋላ በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ወደ መሪዎች ይጠጋል።
የደረጃ ለውጥ የሚያስከትለው የፋሲል ከነማ እና የመቻል ጨዋታ ተጠባቂ ኾኗል።
ባሕርዳር ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ ነው።
ሁለቱ ክለቦች በውጤት ማጣት ውስጥ ነው የሚገኙት። የዛሬውን ጨዋታ የሚሸንፈው ክለብ ደረጃውን ማሻሻል ይችላል።
በሌሎች ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና ከሸገር ከተማ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9፡00 ይጫወታሉ። የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከሽረ ምድረ ገነት የሚያደርጉት ጨዋታ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here