ባሕር ዳር፡ የካቲት 30/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ምድብ “ለ” ላይ የሚገኘው ደሴ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማን 6ለ0 በኾነ ሰፊ ልዩነት በማሸነፍ የከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” መሪ ኾኗል።
በሃዋሳ ሰው ሠራሽ ሳር በተነጠፈለት ሜዳ የተደረገውን ጨዋታ ደሴ ከተማ በፍጹም የበላይነት ነው ያጠናቀቀው።
ቅኝቶቹ (ደሴ ከተማ) ማሸነፉን ተከትሎም ነጥቡን 22 በማድረስ ሃላባ ከተማን በግብ ክፍያ በመብለጥ ነው መሪ የኾነው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



