ከሰሞኑ በተደረጉ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

0
60
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከሰሞኑ በተለያዩ ከተሞች በተደረጉ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት አሸንፋለች ። አትሌት ፅጌ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ ወስዶባታል።
አትሌት ግርማዊት ገብረ እግዚአብሔር በ1 ሰዓት 07 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ 5ኛ ወጥታለች።
በፈረንሳይ ዴ ሁካ ሰሚ ደ ፓሪስ የግማሽ ማራቶን አትሌት ፍታው ዘርኣይ በቀዳሚነት ውድድራን ፈፅማለች ።
አትሌቷ የገባችበት 1 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ የቦታው ምርጥ ሰዓት ነው።
ጃፓን ናጎያ ሴቶች ማራቶን አትሌት ዓይናለም ደስታ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በአምስት ወር ውስጥ ሁለተኛ ማራቶኗን የተካፈለችው አትሌት ዓይናለም ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 22 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ እንደወሰደባት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here