በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
65
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ባሕርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
ባሕርዳር ከተማ ዛሬ ከነገሌ አርሲ ጋር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚያደርገው ብርቱ ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡
በሊጉ 22 ጨዋታዎችን አድርጎ በ27 ነጥብ 11ኛ ደረጃ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ ዛሬ ከ22 ጨዋታ 37 ነጥብ በማስመዝገብ ሦሥተኛ ደረጃ ከሚገኘው ነገሌ አርሲ ጋር የሚያደርገው ፉክክር በጉጉት ይጠበቃል።
ባሕር ዳር ከተማ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ደረጃውን ያሻሽላል፡፡ ባሕረዳር ከተማ በ22ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና 2ለ0 መሸነፉ ይታወሳል። ጨዋታው ቀን 9፡00 ይካሄዳል፡፡
ፋሲል ከነማ ከሽረ ምድረገነት ጋር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ጨዋታው ቀን 9፡00 ይካሄዳል።
ፋሲል ከነማ 22ኛ ሳምንት በአለቀ ደቂቃ በራስ ላይ በተቆጠረ ግብ በሲዳማ ቡና 1ለ0 መሸነፉ ይታወሳል። ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር ከተለያየ በኋላ በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በዛሬው ጨዋታ የሚያስመዘግበው ውጤት ይጠበቃል።
በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ከሀድያ ሆሳዕና በሀዋሳ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲጫወቱ፣ ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ይጫወታሉ። ጨዋታዎቹ ምሽት 12፡00 ይደረጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here