ደሴ ከተማ መሪ የሚኾንበትን ነጥብ ለማስመዝገብ ይጫወታል።

0
65
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 13 ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምድብ “ለ” ላይ የሚገኘው ደሴ ከተማ ወሳኝ ጨዋታውን ያደርጋል።
በሃዋሳ ሰው ሠራሽ ሳር በተነጠፈለት ሜዳ ቀን 7:30 ደሴ ከተማ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር ነው የሚጫወተው።
ቅኝቶቹ ( ደሴ ከተማ) በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ጨዋታን በድል መጀመሩ ይታወሳል።
ቡድኑ 19 ነጥብ እና 10 የግብ ክፍያ በመያዝ ከመሪው ሃላባ ከተማ በሦሥት ነጥብ ብቻ ርቆ በሁለተኛነት ተቀምጧል።
የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈም ሃላባ ከተማን በሁለት ንጹህ የግብ ክፍያ በመብለጥ የከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ”ን መምራት ይችላል።
ከጨዋታ_ ጨዋታ አቅሙን እያሳደገ እና የአጨዋወት ዘዴውን እያሻሻለ የሚገኘው ደሴ ከተማ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ይፈተናል ተብሎ አይጠበቅም።
ጨዋታውን በማሸነፍም መሪ ይኾናል የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች በርካቶች ናቸው።
ቀን 7:30 የሚካሄደውን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ፊፋ ፕላስ በቀጥታ እንደሚያስተላልፈው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በድረ ገጹ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here