በኤፍ ኤ ዋንጫ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ዛሬ ይጫወታሉ።

0
50

 

ባሕር ዳር: የካቲት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ ዛሬ አምስተኛ ዙር ላይ አንድ ጨዋታ ይካሄዳል። ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረስ በሜዳው ሊቨርፑልን ምሽት 5:00 ላይ ይጋብዛል።

ዎልቭስ እና ሊቨርፑል በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ተገናኝተው ወልቭስ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ ኧርኔ ስሎት ለእኛ የፕሪምዬር ሊጉም ኾነ የኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታዎች አስፈላጊዎች ናቸው ብለዋል። ዎልቭስ በሊጉ ግርጌ ላይ ቢቀመጥም ዝቅተኛ ግምት ሰጥተው ወደ ጨዋታው እንደማይሄዱ ተናግረዋል።

በኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታ አሸናፊ ስንኾን ሻምፒዮን የምንኾንበት እድል ይዞ ስለሚመጣ ዛሬ ለማሸነፍ እንጫወታለን ነው ያሉት አሠልጣኙ።

የዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ አሠልጣኝ ሮብ ኤድዋርድስ” በጨዋታው እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል የሚያግዘንን ልምምድ ሠርተናል፤ ከተጨዋቾች ጋር ሃሳብም ተለዋውጠናል” ብለዋል። ዓላማቸው ማሸነፍ ብቻ እንደኾነም ገልጸዋል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here