የአስቶን ቪላ እና የቼልሲ ፍልሚያ ዛሬ ተጠባቂ ነው።

0
64

 

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ ግብ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በተለይ አስቶን ቪላ በቪላ ፓርክ ምሽት 4:30 ላይ ቼልሲን የሚጋብዝበት ጨዋታ ይጠበቃል።

አስቶን ቪላ ከ28 ጨዋታዎች 51 ነጥብ በመሠብሠብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቼልሲን ድል ካደረገም የሦስተኛ ደረጃን ከማንቸስተር ዩናይትድ በመረከብ በቻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድሉን የሚያሰፋ ይኾናል።

ተጋጣሚው ቼልሲ ከ28 ጨዋታዎች 45 ነጥብ እና 16 የግብ ክፍያ በመያዝ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን 48 በማድረስ ሊቨርፑልን በግብ ክፍያ በመብለጥ የአምስተኛ ደረጃን ይይዛል።

ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ1995 ወዲህ በ55 ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። ቼልሲ በ28 ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይነት ታሪክ አለው። አስቶን ቪላ ቼልሲን ድል ያደረገው በ14 ጨዋታዎች ሲኾን በ13 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ዛሬስ ማን ያሸንፍ ይኾን? ምሽት 4:30 ላይ የሚደረገው ጨዋታ ምላሹን ይሰጠናል።

በተመሳሳይ ምሽት 4:30 ላይ፦
👉ብራይተን ከአርሰናል
👉ፉልሃም ከዌስት ሃም
👉ማንቸስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት
እንዲሁም ምሽት 5:15 ላይ ደግሞ
👉ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ይጫዎታሉ።

በዋሴ ባዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here