ባሕር ዳር፡ የካቲት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን የንጉሥ ዋንጫ በመጀመሪያው ጨዋታ በአትሌቲክስ ማድሪድ 4ለ0 የተሸነፈው ባርሴሎና በመልሱ ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ውጤቱን ይቀለብሰው ይኾን ? የሚለው ተጠብቆ ነበር።
ከመልሱ ጨዋታ አስቀድሞ የባርሴሎና አሠልጣኝ እና ተጨዋቾች ውጤቱን መቀልበስ የሚያስችል አቅም እና ታሪክ እንዳላቸው ገልጸው ነበር። ጨዋታውም የተለየ ግምት የሚሰጠው እና ታሪካዊ እንደኾነ ሲገለጽ ነበር።
ነገር ግን ባርሴሎና የ4ለ0 ውጤቱን መቀልበስ ሳይችል ቀርቷል። በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 3ለ0 ቢያሸንፍም በድምር ውጤት 4ለ3 ተሸንፎ ለፍጻሜ ሳይደርስ ቀርቷል።
ለፍጻሜ የደረሰው አትሌቲኮ ማድረግ ከሪያል ሶሲዳድ እና አትሌቲክ ቢልባዎ አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይጨወታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!



