ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ዎልቭስ ከሊቨርፑል ምሽት 5:15 የሚያደርጉት ጨዋታ የደረጃ ለውጥ የሚያስከትል ነው።
ሊቨርፑል 48 ነጥብ እና 10 ንጹህ የግብ ክፍያ በመያዝ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደግሞ ነጥቡን 51 በማድረስ አስቶን ቪላን በግብ ክፍያ በመብለጥ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ ይላል። በመኾኑም ጨዋታው ለቀዮቹ ወሳኝነት አለው።
የሊቨርፑል አሠልጣኝ ስሎት “ዎልቭስ በሜዳው ጠንክሮ እንደሚጫዎት እናውቃለን። እኛ ደግሞ ጨዋታውን ማሸነፍ ለፕሪሚየር ሊጉ ብቻ ሳይኾን ለሌሎች ሊጎችም ያስፈልገናል። እናም ግባችን ማሸነፍ ነው” ብለዋል።
ወልቭስ ከ29 ጨዋታዎች 13 ነጥብ ብቻ በመያዝ በሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2004 ወዲህ በ23 ጨዋታዎች ተገናኝተው ሊቨርፑል በ19 ጨዋታዎች አሸንፏል።
ወልቭስ በሁለት ጨዋታ ብቻ ያሸነፈ ሲኾን በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ ምሽት 4:30 ላይ ይካሄዳሉ። በዚህም መሠረት፦
👉ቦርንማውዝ ከብሬንትፎርድ
👉ኤቨርተን ከበርንሌይ
👉ሊድስ ከሰንደርላንድ የዛሬ መርሐ ግብሮች ናቸው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



