ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን የንጉሡ ዋንጫ ምሽት 5:00 ባርሴሎና በካምፕ ኑ ስታዲየም ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ለግማሽ ፍጻሜ ይጫወታል።
በመጀመሪያው ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ሚትሮፖሊታኖ ስታዲየም ባርሴሎናን 4ለ0 ማሸነፉ ይታዎሳል።
የባርሴሎናው አሠልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ የማይቻል የሚመስለውን ውጤት የመቀልበስ ጨዋታ አድርጎ ለማሳየት ሌሎች ተጫዋቾች ከላሚን ያማል በላይ መጫዎት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
“ቡድናችን ዛሬ ማሸነፍ ብቻ ሳይኾን በመጀመሪያው ዙር የደረሰበትን ሽንፈት ማጣፋት ይጠበቅበታል ነው ያሉት አሠልጣኙ።
በዛሬው ጨዋታ ማርከስ ራሽፎርድ እና ራፊና እንደሚሰለፉ አሠልጣኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።
ኢ.ኤስ.ፒ.ኤን እንዳስነበበው ባርሳ በመጀመሪያው ዙር 4ለዐ በመሸነፉ የዛሬው ጨዋታ የተራራ ያህል ገዝፎበታል። ያም ኾኖ ላሚን ያማል ከሰሞኑ ከቪያሪያል ጋር በነበረው ጨዋታ ሃትሪክ መሥራቱ ለዛሬው ጨዋታ ይበልጥ ያበረታዋል ሲል አትቷል።
ባርሴሎና ለፍጻሜ ለመድረስ አምስት እና ከዚያ በላይ ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡
የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሠልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ በበኩላቸው የንጉሡ ዋንጫን በሚያምር ሁኔታ አስቀጥለነዋል። ዛሬ ሁለት ዕድል ይዘን ብንጫወትም ማሸነፍ የመጀመሪያ ግባችን ነው ብለዋል።
በዛሬው ጨዋታ ፓብሎ ባሪዮስ እንደማይሰለፍም ሲሞኔ ተናግረዋል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



