ባሕር ዳር: የካቲት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይት ኤቨርተንን 1ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግሩም ብቃት ያሳየው ግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ የጨዋታው ኮከብነትን አግኝቷል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ጠንካራ የኾነውን ኤቨርተንን እንዲያሸንፍ ትልቁን ድርሻ ወስዷል።
ግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ በጨዋታው መጨረሻ ላይ የኤቨርተኑ ተከላካይ ማይክል ኪን ግብ ልትኾን የምትችል ኳስ አግኝቶ በግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ ድንቅ ብቃት መክናለች።
ግብ ጠባቂው መረብ ላይ ማረፍ የሚችሉ አራት ኳሶችን በማዳን ዩናይትድን ከሽንፈት የታደገ የጨዋታው ኮኮብ በሚል ሽልማቱን ማግኘት ችሏል።
እናንተስ ጨዋታውን እንዴት አገኛችሁት?
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



