ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ይጫወታል።

0
60
ባሕር ዳር: የካቲት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ የደረጃ ለውጥ የሚደረገበት ጨዋታ ይደረጋል።
ምሽት 5:00 ኤቨርተን በሂል ዲንክሰን ስታዲየም ማንቸስተር ዩናይትድን ይጋብዛል።
ኤቨርተን ካደረጋቸው 26 ጨዋታዎች 37 ነጥብ በመያዝ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቡድኑ ዛሬ የሚያደርገውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን 40 በማድረስ አንድ ደረጃ የሚያሻሽል ይኾናል። ቡድኑ አቻ ቢለያይም ደረጃውን ከፍ የሚያደርግ ይኾናል።
ተጋጣሚው ማንቸስተር ዩናይትድ ከ26 ጨዋታዎች 45 ነጥብ በመሠብሠብ ደረጃው አምስተኛ ነው። ቀያይ ሰይጣኖች ጨዋታውን የሚያሸንፉ ከኾነ ደረጃቸው ከፍ ይላል።
ሁለቱ ቡድኖች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ61 ጨዋታዎች ተገናኝተው ማንቸስተር ዩናይትድ በ38 ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይ ነው።
ኤቨርተን ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፈው በዘጠኝ ጨዋታዎች ብቻ ነው። በ14 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል ሲል ያስነበበው ኤአይስኮር ነው።
ለኤቨርተን ጃክ ግሪሊሽ እና ጃክ ኦብሪን አይሰለፉም፡፡
ለማንቸስተር ዩናይትድ ማቲያስ ዴሊክ፣ ሜሰን ማውንት እና ፓሪክ ዶርጉ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ሊጉን አርሰናል ይመረዋል። ማንቸስተር ሲቲ በሁለተኛነት ሲከተል አስቶን ቪላ በሦስተኛነት ተቀምጧል።
ዌስት ሃም፣ በርንሌይ እና ዎልቭስ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here