👉ጥቂት ነጥቦች ከዛሬው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ በፊት፦

0
64

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት15/2018ዓ.ም (አሚኮ) -ቶትንሃም በ27ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 1፡30 ላይ በሜዳው የሊጉን መሪ አርሰናልን ያስተናግዳል፡፡

-ሁለቱ ክለቦች በደረጃ ሰንጠረዡ አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ በሁለት ነጥብ ልዩነት ሊጉን እየመራ ቶትንሃም በበኩሉ ከወራጅ ቀጠና በአምስት ነጥብ ከፍ ብሎ 16ኛ ላይ ኾኖ ነው የሚገናኙት፡፡

-አርሰናልና ቶትንሃም እስከዛሬ 212 ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡

-መድፈኞቹ 90 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነት ሲኖራቸው ቶትንሃም 67 ጨዋታዎችን አሸንፏል፡፡ ቀሪ 55 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅዋል፡፡

-ከ2021 ወዲህ ያለው የ10 ጨዋታዎች ግንኙነታቸው ብቻ ሲታይ ደግሞ ቶትንሃም ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ አርሰናል ስምንት ጊዜ ሲረታው አንድ ጨዋታ የአቻ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

-ባለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ቶትንሃምን ያሸነፈው አርሰናል እ.አ.አ ከ1987 እስከ 1989 ካስመዘገበው ወዲህ የለንደን ተቀናቃኙን ለመጀመሪያ ጊዜ በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ለማሸነፍ ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

-ቶትንሃም በበኩሉ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሜዳው በአርሰናል የደረሰበትን ሽንፈት ለመቀልበስ ይፋለማል፡፡

-ሁለቱ ክለቦች በዚህ ዓመት በተገናኙበት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ አርሰናል በኤብሪች ኢዜ ሀትሪክ ታግዞ 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።

-ለአዲሱ የቶትንሃም አሠልጣኝ ኢጎር ቱዶር የዛሬው ግጥሚያ አዲሱን ክለባቸውን የሚመሩበት የመጀመሪያ ጨዋታቸው ነው፡፡

-ከዚህ በፊት አዲስ የቶትንሃም አሠልጣኝ ኾነው በመጀመሪያ ጨዋታቸው አርሰናልን ያገኙት ሰው ግሌን ሆድል ሲሆኑ በሚያዚያ ወር 2001 በኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ በተገናኙበት በዚያ ጨዋታ በአርሰናል 2 ለ 1 ተሸንፈዋል፡፡

-ኾኖም የአሁኑ የቶትንሃም አሠልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከዚህ በፊት አዲስ ክለብ ይዘው ያደረጓቸውን የመጀመሪያ አምስት ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፈዋል፡፡ ዛሬስ?

በሃይሌ አበራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here