ሪያል ማድሪድ መሪነቱን ማጠናከር የሚያስችለውን ጨዋታ ያደርጋል።

0
16

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የላሊጋው መሪ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን ለማስፋት ከኦሳሱና ጋር ምሽት 2፡30 የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ሪያል ማድሪድ በ60 ነጥብ ላሊጋውን እየመራ ይገኛል። ባርሴሎና ደግሞ በ58 ነጥብ ይከተላል። ዛሬ ሪያል ማድሪድ ካሸነፈ ባርሴሎና እስከሚጫወት ድረስ መሪነቱን ከሁለት ነጥብ ወደ አምስት ነጥብ ያሰፋል።

በሪያል ማድሪድ በኩል ወሳኝ የኾኑት ቤሊንግሃም እና ኤደር ሚሊታኦ አይሰለፉም።

ተጋጣሚው ኦሳሱና ከ24 ጨዋታዎች 30 ነጥብ በመያዝ 10ኛ ጀረጃ ላይ ይገኛል።

ዛሬ ጨዋታውን ካሸነፈ አንድ ደረጃ ከፍ የሚል ይኾናል።

በሌሎች ጨዋታዎች፦ ሪያል ሶሴዳድ ከሪያል ኦቪዶ ቀን 9:00 ይጫወታሉ።

ሪያል ቤቲስ ከሪያል ቫይካኖ ምሽት12:15 ሲጫወቱ ምሽት 5:00 ደግሞ አትሌቲኮ ማድሪድ ከኢስፓኞል ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይኾናል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here