በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
12

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ቀን 9:00 በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታል።

ባሕር ዳር ከተማ ከ19 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአራት ጨዋታዎች ብቻ ነው። በ12 ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በሦስት ጨዋታ ደግሞ ተሸንፎ 24 ነጥብ እና አንድ የግብ ክፍያ በመያዝ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የቡድኑ ሥራ አሥኪያጅ ልዑል ፈቃዱ ለአሚኮ ዲጂታል እንደተናገሩት ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ያስመዘገበው ውጤት አስደሳች አይደለም።

ቡድኑ በተከላካይ፣ አማካይ እና በመሥመር በኩል ጥሩ አሰላለፍ ቢኖረውም የአጥቂው ክፍል ግን ደካማ እንደነበር ተናግረዋል።

ቡድኑ ከ20ኛው ሳምንት መርሐ ግብር ጀምሮ ውጤታማ ይኾን ዘንድም ኹነኛ አጥቂዎችን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን ነው ሥራ አሥኪያጁ የተናገሩት። ዛሬ ወደ አሸናፊነት እንደሚመለስ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

ባሕር ዳር ከተማ ዛሬ ካሸነፈ ደረጃውን ከፍ ያደርጋል።

ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና ከ19 ጨዋታዎች 24 ነጥብ በመያዝ በባሕር ዳር ከተማ በግብ ክፍያ ብቻ ተበልጦ 10ኛ ደረጃ ላይ ነው።የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ደረጃውን ከፍ ያደርጋል።

ምሽት 12:00 ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ ቀን 9:00 ወላይታ ዲቻ ከመቻል ምሽት 12:00 ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ የሚጫወቱ ይኾናሉ።

ሊጉን ሲዳማ ቡና፣ ሃዋሳ ከተማ እና ነገሌ አርሲ በቅደም ተከተል እየመሩት ይገኛሉ።

መቀሌ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ድቻ እና አርባ ምንጭ ከተማ ከ17 እስከ 20ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here