ባሕርዳር: የካቲት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ውድድር አዳማ ላይ እየተካሄደ ነው።የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ከተማና ሜዳ አልታወቀም ነበር።
ከየካቲት 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለተኛው ዙር ውድድሮች የሚጀምሩ ሲኾን፣ በድሬድዋ ከተማ ድሬድዋ ሜዳ ላይ ጨዋታዎች እንደሚከወኑ ታውቋል።የጨዋታ መርሐ ግብሮች ለወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!