አርሰናል መሪነቱን ማስፋት የሚችልበትን ጨዋታ ያደርጋል።

0
54
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ምሽት 5:00 ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ በሜዳው ሞሊኒክስ ስታዲየም ከአርሰናል ጋር ይጫወታል።
ሊጉን በ57 ነጥብ እየመሩ የሚገኙት መድፈኞቹ ጨዋታውን ካሸነፉ ነጥባቸውን 60 በማድረስ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ያሰፋሉ።
ይህም ዋንጫውን ለማሸነፍ ያላቸውን እድል እንዲያሳፉ ያደርጋቸዋል። የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ሊጠናቀቅ 12 ጨዋታዎች ብቻ መቅረቱን ልብ ይሏል።
አሠልጣኝ አርቴታ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ካይ ሀቨርዝ በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፉ ተናግረዋል።
ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ ከ26 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። ዘጠኝ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዎልቭስ ጨዋታውን ቢያሸንፍ ካለበት 32 የግብ ዕዳ ላይ መቀነስ ይችል እንደኾነ እንጅ የደረጃ ለውጥ አያስገኘውም።
ሊጉን አርሰናል በ57 ነጥብ እየመራው ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ በ53 ነጥብ በሁለተኛነት ተቀምጧል። አስቶን ቪላ ደግሞ በ50 ነጥብ ሦሥተኛ ደረጃን ይዟል።
ዌስት ሃም፣ በርንሌይ እና ዎልቭስ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here