ባሕር ዳር: 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ አራተኛ ዙር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በጨዋታዎቹ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች በታችኛው ዲቪዚዮን ቡድኖች ከመፈተን ባለፈ ነጥብ ሊጥሉ ይችላሉ ሲል ዴይሊ ስፖርት አስነብቧል።
ምሽት 1:30 ላይ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሰናል በሊግ አንድ ከሚሳተፈው ዊጋን አትሌቲክ ጋር በኤሚሬትስ ስታዲየም ይጫወታል።
ሁለቱ ቡድኖች በኤፍ ኤ ዋንጫ ታሪክ በአንድ ጨዋታ ተገናኝተው በአቻ ውጤት ነው የተለያዩት። ዛሬስ? ምሽት 1:30 ላይ የሚደረገው ጨዋታ ምላሹን ይሰጣል።
አሠልጣኝ አርቴታ ለጨዋታው እንደማንኛውም ጨዋታ ትኩረት ሰጥተን ቋሚ ተሰላፊዎችን እንጠቀማለን ብለዋል።
ከብሬንትፎርድ የአቻ ውጤት በኋላም ዛሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እንጫወታለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



