ምሽት የተደረጉ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ውጤቶች

0
80
ባሕር ዳር: የካቲት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ የኤፍ ኤ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታ ምሽት ላይ ሰባት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
ማንቸስተር ሲቲ ሳልፎርድን 2ለ0 ረቶ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል። በጨዋታውም ዶሪንግተን በራሱ መረብ ላይ እና ጉሂ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሊቨርፑልም ብራይተንን 3ለ0 አሸንፏል። የማሸነፊያ ግቦቹንም ጆንስ፣ ሰቦዝላይ እና መሐመድ ሳላህ ናቸው ያስቆጠሩት።
ኒውካስትል አስቶንቪላን 3ለ1 ሲረታ ቶናሊ እና ዋልትሜድ ለአሸናፊው በድን ግቦችን አስገኝተዋል። የአስቶቪላን ብቸኛ ግብ ደግሞ ታሚ አብርሃም አስቆጥሯል።
ዌስትሀም፣ ማንስ ፊልድ ታውን፣ ኖርዊች እና ሳውዛምፕተንም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻሉ ቡድኖች ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here