በስፔን የንጉሡ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ ዛሬ አትሌቲኮ ማድሪድ ከባርሴሎና የሚጫወቱ ይኾናሉ።

0
51
ባሕር ዳር: የካቲት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጨዋታው ከ70 ሺህ በላይ ተመልካች በሚይዘው በግዙፉ የሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ምሽት 5:00 ይካሄዳል።
ሁለቱ ቡድኖች በንጉሡ ዋንጫ ከዚህ ቀደም ለስምንተኛ ጊዜ ተገናኝተዋል።
ባርሴሎና በስድስት ጨዋታዎች በማሸነፍም የበላይነቱን አስመስክሯል። በሁለት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ እንደ አውሮፓ አቆጣጣር ከ2003 ወዲህ በንጉሡ ዋንጫ ባርሴሎናን አሸንፎ አያውቅም።
በ2025/2026 የውድድር ዘመን ባርሴሎና የላ ሊጋው መሪ ሲኾን አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ ሦስተኛ ላይ ነው። በመኾኑም ሁለቱም ቡድኖች እያሳዩት ከሚገኙት ወቅታዊ አቋም አንጻር ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል።
ትናንት በተደረገ የንጉሡ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ሶሴዳድ አትሌቲክ ክለብን 1ለ0 ማሸነፉ ይታዎሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here