“አርሰናልን መግጠም አያስጨንቀንም” አሠልጣኝ ኪት አንድሪውስ

0
84
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 5:00 ብሬንትፎርድ በሜዳው ጌቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም አርሰናልን ይጋብዛል።
ሊጉን በ56 ነጥብ እየመራ የሚገኘው አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አንድ እጁን ዋንጫው ላይ አሳርፎ የድል ጉዞውን ለማስቀጠል ያስችለዋል።
አርሰናል ዛሬ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ሊያጣ ስለሚችል በጨዋታው ይፈተናልም እየተባለ ነው።
ሚካኤል ሜሪኖ በጉዳት ከስብስቡ ውጪ መኾኑን አሠልጣኝ አርቴታ አረጋግጠዋል።
ቡካዩ ሳካ እና ማርቲን ኦዴጋርድም ላይሰለፉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል። የፊት መስመሩን ቪክቶር ዮኬሬስ የመረዋል ነው የተባለው።
ተጋጣሚው ብሬንትፎርድ ከ25 ጨዋታዎች 39 ነጥብ በመያዝ ሰባተኛ ላይ ተቀምጧል። ጨዋታውን ማሸነፍ ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግ ያግዘዋል።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2018 ወዲህ በ11 ጨዋታዎች ተገናኝተው አርሰናል በስምንት ጨዋታዎች አሸንፏል።
ብሬንትፎርድ አርሰናልን ያሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። በሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
የብሬንትፎርድ ዋና አሠልጣኝ ኪት አንድሪውስ “የዛሬው ጨዋታ ከባድ መኾኑን ብናውቅም ምንም ሳንጨነቅ ለውጤት እንጫወታለን” ነው ያሉት።
ፋቢዮ ካርቫልኾ እና አንቶኒ ሚላምቦ ለብሬንትፎርድ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here