ባሕር ዳር፡ የካቲት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አምስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
ማንቸስተር ሲቲ ፉልሀምን 3ለ0 ሲያሸንፍ የማሸነፊያ ግቦቹን ሰሚኒዮ፣ቸርኪ እና ሀላንድ አስቆጥረዋል።
በሌላ ጨዋታ ሊቨርፑል ወደ ስታዲየም ኦፍ ላይት ተጉዞ ሰንደርላንድን በቫን ዳይክ ግብ 1ለ0 አሸንፎ ተመልሷል።
አስቶንቪላ ደግሞ ብራይተንን 1ለ0 ሲያሸንፍ ሂምሽል ውድ የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
በርንለይም ክርስታል ፓላስን 3ለ2 አሸንፏል። ግቦቹንም ማጅብሪ፣ አንቶኒ እና ለርማ በራሱ ግብ ለበርንለይ ሲያስቆጥሩ የክርስታል ፓላስን ሁለቱንም ግቦች ስትራንድ ላርሰን አስቆጥሯል።
ኖቲንግሀም ፎረስት እና ወልቨስ ደግሞ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



